Monday, October 7, 2024
spot_img

በመቐለ ከተማ ከ18 ወራት በኋላ ትምህርት ሊጀመር ነው ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ጳጉሜን 3፣ 2013 ― በትግራይ ክልል መቀመጫ የመቐለ ከተማ ባለፈው ዓመት አጋማሽ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እንዲሁም እሱን በተከተለው ጦርነት ሰበብ ለ18 ወራት ተቋርጦ የነበረው የትምህርት ሒደት ሊጀመር መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ማስታወቁን የአሜሪካ ድምጽ ዘግቧል፡፡

በከተማው በአዲስ ዓመት ትምህርት ይጀመራል መባሉን ተከትሎም ምዝገባ እየተካሄደ እንደሚገኝ ነው የተነገረ ሲሆን፣ ይኸው ነሐሴ 25፣ 2013 የጀመረው የትምህርት ምዝገባ እስከ መስከረም 9፣ 2014 ድረስ ይቀጥላል ተብሏል፡፡

በክልሉ መቀመጫ ትምህርት ይጀመራል ቢባልም ባለፉት ሦስት ወራት ግን የመምህራን ደመወዝ እንዳልተከፈለም ዘገባው አመልክቷል፡፡

ሆኖም ለመምህራኑ ደመወዝ ባይከፈልም ትምህርት ይጀመራል መባሉን ተከትሎ በጥሩ መነቃቃት ለማስጀመር ፍላጎት እንዳላቸው ለራድዮ ጣቢያው የተናገሩ መምህር አሳውቀዋል፡፡

በትግራይ ክልል በጥቅምት ወር መጨረሻ የጀመረውን ጦርነት ተከትሎ በርካታ ትምህርት ቤቶች መውደማቸው ሲነገር፣ አንዳንዶቹ ትምህርት ቤቶች ደግሞ መጠለያ ጣቢያ ተደርገው እንደነበር መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img