Monday, October 7, 2024
spot_img

የዩናይትድ ኪንግደም ፓርላማ በትግራይ ክልል ጉዳይ ሊመክር ነው

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ጳጉሜን 2፣ 2013 ― የዩናይትድ ኪንግደም ፓርላማ በነገው እለት በትግራይ ክልል ሁኔታ ላይ ሊመክር መሆኑን አሳውቋል።

የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ኮሚቴ ሰብሳቢዋ ሳራህ ቻምፒዮን ይመሩታል በተባለው ስብሰባ ላይ በክልሉ የቀጠለው የሰብአዊ ቀውስ ጉዳይ እንደሚነሳ ነው የተገለጸው።

እርሳቸው የሚመሩት ኮሚቴ በሚያዝያ ወር የዩናይትድ ኪንግደም መንግስት ሁሉንም የዲፕሎማሲ አማራጭ እንዲያወስድ ምክር ሐሳብ ማቅረባቸውን ያስታወሱት ሰብሳቢዋ፣ የአሁኑ ምክክርም በትግራይ ያለው ሁኔታ ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የሚረዳ መሆኑን አመልክተዋል።

እንደ ረድኤት ድርጅቶች መረጃ ከሆነ በትግራይ ክልል ከአምስት ሚሊዮን በላይ ሰዎች ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img