Sunday, October 6, 2024
spot_img

በቤኒሻንጉል ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከ40 በላይ ሰዎች መገደላቸው ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ጳጉሜን 2፣ 2013 ― በቤኒሻንጉል በካማሺ ዞን ምዥጋ በተባለ ወረዳ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከ40 በላይ ሴቶች በታጣቂዎች መገደላቸውን የቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል የሴቶች፣ ወጣቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ገልጧል፡፡

የቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ አበራሽ ደጃሽ እስከ ቅዳሜ ድረስ ጉሙዝን ነጻ እናወጣለን ብለው በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ሰዎች በወረዳው ደዴሳ በተባለ ስፋራ መገደላቸውን መናገራቸውን ዶይቸ ቬለ ዘግቧል፡፡

በቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ እና ምክትል ኮሚሽነር የሆኑት ኢንስፔክተር ምስጋናው ኢንጅፋታ በካመሺ ዞን ድዴሳ በሚባል ስፋራ ያለው የጸጥታ ሁኔታ የከፋ መሆኑንና ከ50 በላይ ሰዎችነ (በብዛት ሴቶች) በታጣቂዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው እና በማጣራት ላይ እንደሚገኙም ተናግረዋል፡፡

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን ሰዳል፣ አጋሎ ሜጢ፣ እና ሚዥጋ በተባሉ ወረዳዎች ውስጥ በታጣቂዎች ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ጥቃቶች መፈጸማቸውን የክልሉ ሴቶች፣ወጣቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ አስታውቀዋል፡፡

የዞኑን ሰላም ለማስፋን የክልሉ አመራሮች በተገኙበት ከዚህ ቀደም የሰላም ጉባኤ መካሄዱን የገለጹ ሲሆን ባለፉው ቅዳሜም በነዋሪው ላይ ጉዳት መድረሱን አብራርተዋል፡፡
በካማሺ ዞን ሚዥጋ ወረዳ ባለፈው ሰኞ ነሐሴ 24 ደግሞ ከ30 በላይ ሴቶች በእነዚሁ ታጣቂዎች በደረሰባቸው ጥቃት በአንድ ስፍራ ህይወታቸው ማለፉንና የወረዳው ነዋሪ በሰላማዊ ሰልፍ ድርጊቱን ማውገዙን አክለዋል፡፡ በወረዳው በታጣቂዎች የሚደረሰውን ጥቃት የፌደራል እና ክልል ጸጥታ ሀይሎች ትኩረት በመስጠት በአስቸኳይ እርምጃ በመውሰድ ማስቆም እንዳለባቸውንም ተናግረዋል፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊና ምክትል ኮሚሽነር ኢንስፐክቴር ምስጋናው እንጅፋታ በዞኑ ያለው የጸጥታ ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን አመልክቷል፡፡ በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ ጸረ ሰላም ያሉት ሀይል በነዋሪ ውስጥ በመደበቅ እና በቤት ውስጥ በመሆን በጸጥታ ሀይሎች ላይ እንደሚተኩስ ገልጸዋል፡፡ ባለፈው ሰኞና ማክሰኞ በዞኑ (ሚዠጋ)ቦሎጅጋንፎይ በተባለ ወረዳ ድደሳ ቀበሌ ውስጥ ከ50 በላይ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ሀላፊው አስረድተዋል፡፡ የዞኑ የጸጥታ ችግርም አሳሰቢ በመሆኑ ተጨማሪ የጸጥታ አስከባሪዎች ወደ ስፋራውን እንዲላኩ መጠየቃቸውንም ኢንስፔከተሩ አክለዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img