አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ጳጉሜን 2፣ 2013 ― ሩዋንዳ በኢትዮጵያ ያለውን ችግር ለመፍታት የሚያስችል ውስጣዊ መፍትሄ እንድታገኝ ከመመኘት ውጭ ብዙ የምታደርገው የተለየ ነገር እንደሌለ ፕሬዝዳንትዋ ፓል ካጋሜ ተናግረዋል፡፡
የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ይህን ያሉት ከሩዋንዳ ብሮድካስቲንግ ኤጀንሲ (አር.ቢ.ኤ) ጋር በነበራቸውና ሰፋ ያሉ ጉዳዮች በተነሱበት ቃለ-መጠይቅ ነው፡፡
ፕሬዝዳንቱ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታና የሩዋንዳ ሚናን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ በመንተራስ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
“ኢትዮጵያ የሩዋንዳ ወዳጅ ነበአች፣ አሁንም ናት፣ ወደፊትም ወዳጅ ሆና ትቀጥላለች” በማለት ንግግራቸው የጀመሩት ፖል ካጋሜ፣ በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ አሕመድ በሩዋንዳ በነበራቸው ጉብኝት ሰፋ ያሉ ጉዳዮች አንስተው መወያየታቸውንም ገልጸዋል፡፡
ፖል ካጋሜ አሁን በኢትዮጵያ ትግራይ እና ትግራይ ክልል በሚያዋስኑ ክልሎችም ግጭት መኖሩን ተከትሎ ያጋጠመውን ችግር ለማቃለል የተለያዩ አካላት ከመንግስት ጋር እየሰሩ መሆናቸው እንዲሁም የሰብዓዊ እርዳታ በማዳረስ በኩልም እየተሰራ መሆኑን እንደሚያውቁ አንስተዋል፡፡
ካጋሜ “ሀገሪቱ ሰላምና መረጋጋት ያስፈልጋታል፤ ይህ ጥያቄ ሌለው ጉዳይ ነው፡ ሀገሪቱ ያጋጠማትን ችግር ለመፍታት ምን እየሰራች ነው የሚለው ደግሞ ዋናው ነገር ነው ብለዋል፡፡
የችግሩ መጠን ከሰፋ ግን ወዳጅና ጎረቤት ሀገራት እንዲሁም የዓለም አቀፉ ማህበረስብ የመፍትሄ አካል ለመሆን መሞከር የተለመደ መሆኑን የገለጹት ፓል ካጋሜ፤ ሩዋንዳ ተቃራኒ ኃይሎች ወደ ጠርጴዛ እንዲመጡ በማድረግ የመፍትሄው አካል ትሆናለችም ብለዋል፡፡
“ፕሬዝዳንቱ ሊኖረን የሚችለው ሚና “ኃሳብ ማወጣትና ማጋራት ነው” ሲሉም ነው የተናገሩት ሲሆን፣ ችግሩ የውስጥ ነው፤ ትግራይ የኢትዮጵያ አካል ናት፤ የሁለት ሀገራት ግጭት እንዳልሆነ መረዳት” እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል መባሉን የዘገበው አል ዐይን ነው፡፡