Saturday, October 5, 2024
spot_img

የድምጻዊ ዓለማየሁ እሸቴ የስንብት ሥነ ሥርዐት በመስቀል አደባባይ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

ባሳለፍነው ዐርብ ሌሊት በልብ ሕመም ህይወቱ ያለፈው በኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ዘርፍ አንጋፋ የነበረው ድምፃዊ ዓለማየሁ እሸቴ የስንብት ሥነ ስርአት በመስቀል አደባባይ እየተከናወነ ይገኛል።

በስንብት ሥነ ስርዓቱ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ ወዳጅ ዘመዶቹ፣ የኪነ ጥበብ ሰዎችና አድናቂዎቹ ተገኝተዋል፡፡

የአርቲስቱ የቀብር ሥነ-ስርዓት ከመስቀል አደባባዩ የክብር ስንብት መርኀ ግብር በኋላ፣ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ ይፈፀማል ተብሏል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img