አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ጳጉሜን 2፣ 2013 ― የብርሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ሰልጣኝ ወታደሮችን አስመርቋል፡፡ የማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ምረቃውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እንዲሁም የሃገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ መኮንኖች በተገኙበት ነው ያካሄደው፡፡
የሁርሶ ወታደራዊ ኮንቲንጀት ማሰልጠኛ በተመሳሳይ ከሁለት ቀናት በፊት ማስመረቁ የሚታወስ ነው፡፡ በዚህ የምረቃ ስነ ስርአት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተገኝተው ነበር፡፡