Monday, October 7, 2024
spot_img

በትግራይ ክልል በምግብ እጥረት ሰበብ የሰዎች ሕይወት ማለፉ ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ጳጉሜን 2፣ 2013 ― በትግራይ ክልል በተከሰተ የምግብ እጥረት ሰበብ 150 ያህል ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ቢቢሲ የሕወሃት የግብርና ጉዳዮች ኃላፊ ናቸው ከተባሉት አቶ አትንኩት መዝገቦ ሰምቻለሁ ብሏል፡፡

በትላንትናው እለት በትግራይ ስላለው የምግብ አቅርቦት የተናገሩት የሰላም ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል የፌዴራል መንግስት በክልሉ የተናጠል የተኩስ አቁም አድርጎ ሲወጣ እህል ትቶ መውጣቱንና ከዚያ በኋላ ባለው ጊዜ እርዳታ በአግባቡ እንዳይከናወን ሕወሓት እንቅፋት ሆነዋል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

የሕወሃት ሰው የሆኑት አቶ አትንኩት መዝገቦ በአሁኑ ወቅት በክልሉ በተከሰተው የምግብ እትረት ሰዎች ዐይናችን እያየ እየሞቱ ነው ማለታቸው ተመላክቷል፡፡

ሆኖም ቢቢሲ ጉዳዩን በተመለከተ በክልሉ የመገናኛ አገልግሎት ባለመኖሩ ማጣራት አለመቻሉን ነው ያመለከተው፡፡

በትግራይ ክልል የእርዳታ አቅርቦትን በተመለከተ የተባበሩት መንግሥት የሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ ግራንት ሌይቲ ባለፈው ሳምንት ከተጠናቀቀ ሁለት ሳምንት እንደሆነ አሳውቀው የነበረ ቢሆንም፣ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ባለፈው እሑድ ከአንድ መቶ በላይ እርዳታ የጫኑ ተሸከርካሪዎች መቐለ ደርሰዋል ብሏል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img