Monday, October 7, 2024
spot_img

የስደተኞች መታወቂያን ይዘው በትግራይ ግጭት ተገኝተዋል የተባሉ ታጣቂዎችን ጉዳይ እያጣራ እንደሚገኝ የመንግስታቱ ድርጅት ገለጸ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ጳጉሜን 1፣ 2013 ― ከሰሞኑ ‹‹በሱዳን የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የነበሩና የስደተኞች ኤጀንሲ መታወቂያ የያዙ ታጣቂዎች ተመልሰው በግጭቱ ሲሳተፉ ተገኙ›› የሚል መረጃ በማህበራዊ ትስስር መድረኮች ተመልክቻለሁ ያለው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ ጉዳዩን እያጣራ እንደሚገኝ አሳውቋል፡፡

ይህንኑ የቢሮው ቃል አቀባይ ኔቨን ክሬቨንኮቪች ታጣቂዎቹ ይዘውት ተገኙ ከተባለው ‹‹የተመድ የስደተኛ መታወቂያ”ጋር በተያያዘ የወጣውን መረጃ ኤጀንሲው እያጣራ›› መሆኑን ነግረውኛል ያለው አል ዐይን ሚዲያ ነው፡፡

ስደተኞቹን የተመለከቱ አዳዲስ መረጃዎች ሲገኙ፣ ከመጠለያ ጣቢያዎች ሲወጡም ሆነ መታወቂያ ካርዳቸው ሲጠፋ የመረጃ ቋታችን የምናዘምንበት በመደበኛ የአሰራር ስርዓት አለን ያሉት ቃል አቀባዩ፣ ስደተኞቹ ወደ ሃገራቸው ለመመለስ ሲወስኑ ስደተኛነታቸውን እንደሚያጡም ጠቁመዋል፡፡

ቃል አቀባዩ ኤጀንሲው “በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ በስደተኞች የተደረገ እንቅስቃሴ” አለመመልከቱንም የገለጹ ቢሆንም፣ “በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ ሆነን የስደት ተመላሾችን የምናረጋግጥበት ሁኔታም የለም” ስለማለታቸውም ተመላክቷል፡፡

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አገኘሁ ተሻገር ሰሞኑን በሱዳን አቅጣጫ መጥተው ‹‹ሽንፋ የተባለ ቦታን ለመያዝ የተንቀሳቀሱ የቅማንትና ሕወሃት ታጣቂዎች መደምሰሳቸው››ን አሳውቀው ነበር፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img