Monday, September 23, 2024
spot_img

ለሕወሓት ሲሰሩ ነበሩ የተባሉ 16 የሠራዊት አባላት ላይ እስከ 18 ዓመት የሚደርስ ፅኑ እስራት ውሳኔ ተላለፈ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ነሐሴ 29፣ 2013 ― የደቡብ ዕዝ ቀዳማዊ ወታደራዊ ፍርድ ቤት የዕዙ የሠራዊት አባላት ሆነው በአሸባሪነት ለተፈረጀው የህወሓት ቡድን ሲሰሩ ነበሩ ባለቸው 16 የሠራዊት አባላት ላይ የፍርድ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ተከሳሽ የሠራዊት አባላቱ ከቀረቡባቸው ክሶች አንዳንዶቹን አስተባብለው የተከራከሩ ሲሆን፣ አንዳንዶቹን አምነዋል ነው የተባለው፡፡

አቃቤ ሕግም የሰነድና የሰው ማስረጃዎችን አቅርቦ የተከራከረ ሲሆን፣ የተከሳሽ ጠበቆች በበኩላቸው ተከሳሽ የሠራዊት አባላቱ ከዚህ ቀደም በርካታ አዎንታዊ ተግባራትን ያከናወኑ እና የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ፍርድ ቤቱ የቅጣት ማቅለያ እንዲያደርግላቸው ጠይቋል።

ወታደራዊ ፍርድ ቤቱ ትላንት ጠዋት ባስቻለው ችሎት በ16 የሠራዊት አባላት ላይ የጥፋተኝነት ብይን ሰጥቷል።

በዚሁ መሠረት ተከሳሾቹ ላይ ዝቅተኛው 2 ዓመት ከ9 ወር ሲወሰን፣ ከፍተኛ የእስር ቅጣት ደግሞ 18 ዓመት ከ8 ወር ተጥሎባቸዋል መባሉን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ዘግቧል፡፡
ወታደራዊ ፍርድ ቤቱ ፍርደኞቹ የእስር ቅጣቱ በወንጀል ድርጊት ተጠርጥረው እጃቸው ከተያዘበት ቀን ጀምሮ በሚታሰብ ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ነው ብይን የሰጠው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img