Monday, November 25, 2024
spot_img

በፈረቃ ሲሰጥ የነበረው ትምህርት ወደ መደበኛው ሒደት ሊመለስ ነው

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ነሐሴ 29፣ 2013 ― በዓለም አቀፍ ደረጃ በተከሰተው የኮቪድ ወረርሽኝ ሰበብ በፈረቃ ሲሰጥ የቆየው ትምህርት ወደ መደበኛው ሒደት ሊመለስ መሆኑ ተነግሯል፡፡

በተጠናቀቀው የትምህርት ዘመን የኮቪድ 19 ወረርሽን ለመከላከል በሚል ቀድሞ ተማሪዎች ሲማሩበት የነበረው የትምህርት ቀናት በሳምንት ወደ ሦስት ቀናት ዝቅ ተደርጎ ሲሠራበት ቆይቷል፡፡

ከቀናት በኋላ በሚጀምረው የአዲስ ዓመት የትምህርት ዘመን ይህ ለአንድ የትምህርት ዘመን የተተገበረው አሠራር ቀድሞ ወደነበረበት ማለትም ከሰኞ እስከ ዐርብ ባሉት ተከታታይ ቀናት ባለው አሠራር እንደሚመለስ በትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ቤት መሻሻል ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ ባለሞያ አቶ ከተማ ቀውይ ነግረውኛል ብሎ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ አስነብቧል፡፡

በ2013 የትምህርት ዘመን የተለያዩ የትምህርት ክፍል ላይ የሚገኙ ተማሪዎች ተከፋፍለው ትምህርት መጀመራቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ይህም አሠራር ታጥፎ በአዲሱ የትምህርት ዘመን ሁሉንም የትህርት ክፍሎች በተመሳሳይ ጊዜ ለማስጀመር ታቅዷልም ነው የተባለው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img