Monday, September 23, 2024
spot_img

በስድስት ቀናት አንድ መቶ ሰዎች በኮሮና ሕይወታቸው አለፈ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ነሐሴ 29፣ 2013 ― በኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ቀናት አንድ መቶ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሰበብ ሕይወታቸውን እንደተነጠቁ የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡

ከእሑድ ነሐሴ 23 ጀምሮ ባሉት በነዚህ ቀናት ከሟቶቹ በተጨማሪ 7 ሺሕ 271 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሲሆን፣ 696 ሰዎች በጸና ታመው ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡

በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የመያዝ ምጣኔ ቀንሷል በተባለበት ከ6 ሳምንታት በፊት ዝቅተኛ የነበረ ሲሆን፣ በዚህ ወቅት የመያዝ ምጣኔው 1.6 በመቶ ሆኖ ተመዝግቦ ነበር፡፡ ነገር ግን በአሁኑ ወቅት ቁጥሩ በመጨመር በአማካይ ወደ 16.5 በመቶ ከፍ ማለቱን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገልጧል፡፡

በአገሪቱ የኮሮና ቫይረስ የመያዝ ምጣኔ እና የጽኑ ታማሚዎች ቁጥር በመጨመሩ በሆስፒታሎች የአስተኝቶ ማከሚያ ክፍሎች፣ አጋዥ የመተንፈሻ መሳሪያ እጥረት እያጋጠመ ይገኛል የተባለ ሲሆን፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከዕለት ወደ ዕለት በከፍተኛ ደረጃ ከመሰራጨቱም በላይ ሰብዓዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ችግሮችን እያስከተለ እንደሚገኝም ነው የተገለጸው፡፡

ይህንኑ የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከልና የሚያስከትለውን ሞት ለማስቆም ኢኒስቲትዩቱ ህብረተሰቡ ለመጪው የአዲስ ዓመት እና ሌሎች ህዝባዊና ኃይማኖታዊ በዓላት የሚፈጠሩ መሰባሰቦችን እንዲቀንስ፣ የኮቪድ-19 ክትባትን እንዲከተብ፣ ለግብይት ከቤት ውጭ በሚኖር እንቅስቃሴ ማስክ ማድረግ እንዲሁም የእጅ ማጽጃ ሳኒታይዘር እንዲይዝ መክሯል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img