Monday, October 7, 2024
spot_img

ያለ ውጭ ምንዛሬ ሸቀጦችን የማስገባት አሠራር ለተጨማሪ ስድስት ወራት ተራዘመ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ነሐሴ 29፣ 2013 ― መንግስት ላለፉት ለስድስት ወራት ፈቅዶት የነበረውን ያለ ውጭ ምንዛሬ ሸቀጦችን የማስገባት አሰራር ለተጨማሪ ስድስት ወራት መራዘሙን አስታውቋል፡፡

ይህንኑ የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ በትላንትናው እለት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ አስታውቀዋል። ክተር ኢዮብ ይህን የተናገሩት መንግስት በሰባት መሰረታዊ የምግብ ሸቀጦች ላይ የቀረጥ እና ታክስ ማሻሻያ ማድረጉን ይፋ ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡

ከትላንት ዐርብ ነሐሴ 28 ጀምሮ ተግባራዊ ተደርጎ ላልተወሰነ ጊዜ እንደሚገኝ የተገለጸው ማሻሻያ የምግብ ሸቀጦች ማለትም ስንዴ፣ ዘይት፣ ስኳር፣ ሩዝ፣ መኮረኒ፣ ፓስታ እና እንቁላልን የሚመለከት ነው፡፡

በማሻሻያው መሰረት ስንዴ ከውጭ ሲገባ ከጉምሩክ ቀረጥ ነጻ የሚደረግ ሲሆን፣ የምግብ ዘይት፣ ስኳር እና ሩዝ ከውጭ ሲገቡ እና በአገር ውስጥ ግብይት ሲፈጸምባቸው ከማንኛውም ቀረጥ እና ታክስ ነጻ እንደሚሆኑ በመግለጫው ላይ ተጠቁሟል።

ፓስታ እና መኮረኒ ሸቀጦችን በተመለከተ ደግሞ ከውጭ ሲገቡ እና በአገር ውስጥ ግብይት ሲፈጸምባቸው ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ እንዲሆኑ መወሰኑ ተገልጿል። የዶሮ እንቁላልም እንዲሁ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ መሆኑ ተብራርቷል።

መንግስት የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር የገንዘብ እና የፊስካል ፖሊሲ ማሻሻያዎችን እና አስተዳደራዊ እርምጃዎችን ሲወስድ መቆየቱን ያስታወሱት ዶ/ር እዮብ፤ አሁን የተደረገው ማሻሻያ የህዝቡን ኑሮ ለማሻሻል እና ገበያውን ለማረጋጋት አይነተኛ ሚና እንደሚኖረው አስረድተዋል። ይህንኑ ማሻሻያ ተግባራዊ ለማድረግም ለገቢዎች ሚኒስቴር እና ለጉምሩክ ኮሚሽን መመሪያ መተላለፉን ገልጸዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img