አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ነሐሴ 28፣ 2013 ― የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማክስ 8 ቦይንግ 737 አውሮፕላኖቹን ከቀጣዩ ዓመት ጥር ጀምሮ እንደገና ወደ በረራ ሊመልስ መሆኑ ተነግሯል፡፡
ቦይንግ ኩባንያ በማክስ 8 አውሮፕላን ላይ ያደረጋቸው ማሻሻያዎች፣ የበረራ ደኅንነትን የሚያረጋግጡ እንደሆኑ የአየር መንገዱ ሥራ አስፈጻሚ ተወልደ ገ/ማርያም ተናግረዋል።
አየር መንገዱ አውሮፕላኖቹን እንደገና ለማብረር የወሰነው፣ ከ2 ዓመት በፊት ለተከሰከሰበት ማክስ 8 አውሮፕላኑ ከቦይንግ ኩባንያ ከፍርድ ቤት ውጭ የካሳ ክፍያ ለማግኘት መስማማቱን ተከትሎ ነው።
አየር መንገዱ በአዲስ አበባ የተለያዩ የአውሮፕላን መገጣጠሚያዎችን ለማምረት የሚያስችለውን ስምምነት ከሰሞኑ ከቦይንግ ኩባንያ ጋር ስምምነት መፈጸሙ መነገሩ አይዘነጋም፡፡