Sunday, October 6, 2024
spot_img

ሕወሓት በኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካና ወታደራዊ ኃይል ሆኖ መቀጠል እንዳይችል ተደርጎ እንዲደመሰስ አቋም እንደተያዘ የመንግሥት ሹሙ ገለጹ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ነሐሴ 28፣ 2013 ― በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀው ሕወሃት በኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካና ወታደራዊ ኃይል ሆኖ መቀጠል እንዳይችል ተደርጎ እንዲደመሰስ አቋም እንደተያዘ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ ገልጸዋል፡፡

መንግስት ይህንን ውሳኔ የወሰነው በአንድ ወገን ሰላም ስለተፈለገ ብቻ ህወሓት ወደ ሰላም ይመጣል ብሎ ስለማያምን መሆኑን ያነሱት ዶ/ር ቢቂላ፤ በዚህ የተነሳም ‹‹ኢትዮጵያውያን የትም፣ መቼም፣ በምንም ዘምተን ይህን ቡድን ከምድረ ገጽ ማጥፋት አለብን ብለው ተነስተዋል›› ብለዋል።

ሚኒስትሩ ከአል ዐይን ጋር ባደረጉት ቆይታ ሕወሓት ‹‹መደራደርን ለማደናገሪያነት እንጂ ለእውነተኛ ሰላም የሚጠቀም›› እንዳልሆነ በማንሳት፣ ቡድኑ ልዩነቶችን በሰለጠነ መንገድ የመፍታት ስነልቦና፣ ብቃት እና ልምድ እንደሌለውም ተናግረዋል።

ሕወሃት ድርድርን የሚጠቀመው ‹‹ትንፋሽ አግኝቶ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብን ለማሳሳት፤ ጊዜ አግኝቶ ኃይል ለማከማቸት እና ሴራውን ለማስቀጠል እንጂ ቁጭ ብሎ ተደራድሮ የትግራይ ሕዝብ ከዚህ በላይ ሰቆቃ አይገባውም በሚል አስቦ አይደለም›› ሲሉም አክለዋል፡፡

የመከላከያ ሠራዊትን የሰሜን እዝ ጥቃት ተከትሎ በትግራይ የጀመረው የፌዴራል መንግስት እና የሕወሃት ጦርነት 10 ወራትን ማስቆጠሩ የሚታወቅ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img