Saturday, November 23, 2024
spot_img

የአውሮፓ ኅብረት በአፍሪካ የተመረቱ የኮሮና ክትባቶችን ለአህጉሩ ለመመለስ ተስማማ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ነሐሴ 28፣ 2013 ― የአውሮፓ ኅብረት በደቡብ አፍሪካ ድርጅት የተመረቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የጆንሰን እና ጆንሰን የኮሮና ክትባቶችን ለአህጉሩ ለመመለስ መስማማቱን በአፍሪካ ኅብረት ለኮሮና የተቋቋመው ልኡክ ተወካይ ገልጸዋል፡፡

የአውሮፓ ኅብረት ሊመልሳቸው ነው የተባሉት የኮሮና ክትባቶች በአፍሪካ አህጉር የተመረቱ ስለሆኑ በዚያው አህጉር ጥቅም ላይ እንዲውሉ መታሰቡንም የአዣንስ ፍራንስ ፕረስ ዘገባ ያመለክታል፡፡

እነዚህ ክትባቶች በዩኤስ ፋርማ ጃያንት ትእዛዝ በደቡብ አፍሪካው አስፔን ፋርማኬር መድሃኒት ፋብሪካ የተመረቱ ሲሆን፣ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ከአውሮፓ ኅብረት ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮንደር ለይን ጋር በጀርመን በርሊን ተገናኝተው ከመከሩ በኋላ ውሳኔው መተላለፉ ነው የተገለጸው፡፡

የአውሮፓ ኅብረት በደቡብ አፍሪካው ድርጅት የተመረቱትን ክትባቶች ከመመለሱ በተጨማሪ በኮንትራቱ መሠረት ያመረታቸውን ሁሉም ክትባቶች ለአፍሪካ እንዲሠራጭ ከውሳኔ ላይ መደረሱን የአፍሪካ ኅብረት ተወካዩ አክለዋል፡፡

እንደ ሲዲሲ አፍሪካ መረጃ ከሆነ በአፍሪካ አህጉር የኮሮና ክትባት ያገኙ ሰዎ ቁጥር ከአጠቃላይ ሕዝቡ 2 ነጥብ 93 በመቶ ብቻ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img