አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ነሐሴ 28፣ 2013 ― የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ጸሐፊ አንቶንዮ ጉቴሬዝ ከአሜሪካ የምሥራቅ አፍሪካ ልዩ መልእክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ መምከራቸው ተሰምቷል፡፡
ጉቴሬዝ እና ፌልትማን በውይይታቸው ወቅት ወቅታዊውን የኢትዮጵያ ጉዳይ ማንሳታቸው የተነገረ ሲሆን፣ የአስቸኳይ ተኩስ አቁምን አንገብጋቢነት እና በጦርነቱ ችግር ውስጥ ለወደቁ ያልተገደበ የሰብአዊ አቅርቦት በሚደርስበት ዙሪያ ተወያይተዋል ነው የተባለው፡፡
በኢትዮጵያ ጉዳይ የመከሩት አንቶንዮ ጉቴሬዝ እና ጄፍሪ ፌልትማን የሚውሏቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጀት እና አሜሪካ በትግራይ ተጀምሮ ወደ አፋር እና አማራ ክልሎች የተዛመተው ጦርነት ከተጀመረ አንስቶ ጦርነቱ መቆም አለበት በሚል ተደጋጋሚ መግለጫዎችን ሲያወጡ መሰንበታቸው የሚታወቅ ነው፡፡