Monday, October 14, 2024
spot_img

አሜሪካ በትግራይ የሰብአዊ አቅርቦት እንዲዘገይ አድርጓል በሚል የፌዴራል መንግስትን ወቀሰች

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ነሐሴ 27፣ 2013 ― የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ባወጣው መግለጫ የፌዴራል መንግስት በትግራይ ክልል የሰብአዊ አቅርቦት እንዲዘገይ አድርጓል በሚል ወቀሳ አቅርቧል፡፡

በትግራይ በአሁኑ ወቅት ያለውን ሁኔታ አስመልክቶ የተናገሩት የአሜሪካ መንግስት ቃል አቀባይ ኒድ ፕራይስ ፣ የክልሉ ሁኔታ ከመቼውም ጊዜ በላይ መባባሱን ገልጸዋል፡፡

ቃል አቀባዩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ እርዳታ ቢሮን ዋቢ አድርገው እንደገለጹት፣ በትግራይ በአሁኑ ወቅት የእርዳታ መጋዘኖች ተራቁተዋል፣ የነዳጅ እና የገንዘብ አቅርቦት ደግሞ እየተሟጠጠ ነው፡፡ በዚሁ ምክንያት በርካቶች ከፊታቸው ረሃብ መጋረጡን አመልክተዋል፡፡

የአሜሪካ መንግስት ቃል አቀባዩ ኒድ ፕራይስ የፌዴራል መንግስትም ሆነ ሕወሃት በክልሉ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው እንዲደርስ ሁኔታዎችን ከማባባስ ውጭ ትርፍ የለውም ያሉትን ግጭት እንዲያቆሙ በድጋሚ ጠይቀዋል፡፡

እንደ መረጃዎች ከሆነ በትግራይ ክልል በአሁኑ ወቅት 5 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img