Saturday, November 23, 2024
spot_img

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ልዩ ሀገር አቀፍ የጸሎት እና ምህላ ጊዜ አወጀ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ነሐሴ 27፣ 2013 ― የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ በወቅታዊ የሀገሪቱ ሁኔታ እና መጪውን የ2014 ዓመት በማስመልከት የሠላም ጥሪና የመልካም ምኞት መግለጫ አስተላልፏል።

በመግለጫው ለወጣቶች እና ወላጆች ለሁሉም የክልልና የፌደራል መንግስት ባለስልጣናት፣ ለመገናኛ ብዙሃን እንዲሁም ለመላው ኢትዮጵያውያን ሠላማዊ እና የሰከነ አካሄድ እንዲከተሉ ጥሪ አቅርቧል።

የጉባኤውን መግለጫ ያቀረቡት ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ፣ በሰሜኑ ክፍል ያለው ጦርነት ከመጀመሩ በፊትም ሆነ ከዛ በኋላ እንደ ሃይማኖት አባቶች ታሪክ የማይረሳው ጥረት ቢደረግም ሊሳካ አለመቻሉን ገልጸዋል፡፡

ይሁን እንጂ ጦርነት አውዳሚ በመሆኑ የሀይማኖት አባቶች የሰላም ጥሪ ለሁሉም ይድረስ ብለዋል።

በኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ በታወጀዉ ሀገር አቀፍ የፀሎትና ምህላ ጊዜ ላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ሀገራቸውን በፀሎት እንዲያስቡም አሳስበዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img