Saturday, September 21, 2024
spot_img

ብሔራዊ ባንክ በባንኮች በኩል የሚገኝ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀም ላይ ማሻሻያ ማድረጉን አሳወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ነሐሴ 26፣ 2013 ― የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንም በሚመለከት መሻሻያ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

በዚሁ መሠረት ቀደም ሲል ባንኮች ከውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት፣ ከዳያስፖራ ሒሳብና ከሌሎችም ምንጮች ከሚያገኙት የውጭ ምንዛሪ 30 በመቶውን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገቢ እንዲያደርጉ የሚያስገድደው መመርያ መሻሻሉን አስታውቋል፡፡ በመሆኑም ከውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትና ከዳያስፖራ ሒሳብ ቀሪ ሆነው ከወጪ ንግድ፣ ከግለሰብ ሐዋላና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ብቻ ከሚገኝ የውጭ ምንዛሪ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገቢ እንዲያደርጉ መወሰኑን ነው የገለጸው፡፡

ይሁን እንጂ ባንኮች ከወጪ ንግድ፣ ከግለሰብ ሐዋላና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ከሚያገኙት የውጭ ምንዛሪ ውስጥ 50 በመቶውን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገቢ እንዲያደርጉ ግዴታ ተጥሎባቸዋል፡፡

የውጭ ምንዛሪ ያስገኘ ማንኛውም የባንክ ደንበኛ ቀደም ሲል በውጭ ምንዛሪ ሒሳብ ውስጥ ያለ ጊዜ ገደብ መያዝ የሚችለው የውጭ ምንዛሪ መጠን ከ31 ነጥብ 5 በመቶ ወደ 40 በመቶ ከፍ እንዲል መወሰኑን ያመለከተው ባንኩ፣ ቀሪውን አሥር በመቶ ባንኮች በውጭ ምንዛሪ እንዲጠቀሙ መደረጉንም ጠቁሟል፡፡

ይህ መመርያ ‹‹የውጭ ምንዛሪ አመንጪ ደንበኞች ሲያገኙት የነበረው ድርሻ አነስተኛ ነው›› የሚለውን ቅሬታ በተወሰነ ደረጃ የሚፈታ፣ የመንግሥትን የውጭ ምንዛሪ ግኝት አቅም በማሳደግ የውጭ ዕዳ ክፍያ ግዴታዎችን ለመወጣት፣ የአገሪቱን ትልልቅ ፕሮጀክቶች ለማገዝና አስፈላጊ የፍጆታ ዕቃዎችን ከውጭ ለማስገባት የሚያስችል መሆኑ እንደታመነበትም አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም ከባንኮች በተደጋግሚ የሚቀርበውንና ‹‹ከውጭ ኢንቨስትመንት፣ ከዳያስፖራ ሒሳብና ከውጭ ብድር የሚገኝ የውጭ ምንዛሪ ተቀንሶ ወደ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገቢ መደረግ የለበትም›› የሚለውን ጥያቄም የሚመልስ እንደሆነም ገልጿል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img