Friday, October 18, 2024
spot_img

በኔዘርላንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር በአሜሪካ የፖለቲካ ጥገኝነት መጠየቃቸው ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ነሐሴ 26፣ 2013 ― በኔዘርላንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት ሚሊዮን ሳሙኤል በአሜሪካን አገር የፖለቲካ ጥገኝነት መጠየቃቸው ተሰምቷል፡፡

የአምባሳደሩ በአሜሪካን አገር ጥገኝነት የመጠየቃቸው ዜና የመጣው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እያካሄድኩት ነው ያለውን ሪፎርም ተከትሎ የተወከሉበት ኤምባሲ ከሚዘጉት መካከል መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ ከደረሳቸው በኋላ መሆኑ ነው የተነገረው፡፡

አምባሳደር ሚሊዮን ሳሙኤል የኤምባሲውን ሠራተኞች ጥለው ከተሰወሩ ከሁለት ሳምንት በላይ እንደተቆጠረ የተነገረ ሲሆን፣ ይህንኑ ተከትሎም በኤምባሲው የሚገኙ ሌሎች ሠራተኞች ደመወዝ እንዳልተከፈላቸውና አንዳንዶቹም በዚያው በኔዘርላንድ ጥገኝነት መጠየቃቸውን የሚያመለክቱ መረጃዎች ወጥተዋል፡፡

በኔዘርላንድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሊዘጋ ነው የመባሉ መረጃ ከመምጣቱ በፊት በአጠቃላይ 20 ሠራተኞች እንደነበሩት ታውቋል፡፡ እነዚህ ሠራተኞች በአሁኑ ወቅት ለአምባሳደሩ መንግሥት ወደተከራየላቸው ቤት ተዛውረዋል ተብሏል፡፡

በኔዘርላንድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሙሉ ለሙሉ እንዲዘጉ ከተወሰነባቸው መካከል ነው፡፡ አገልግሎት ካቋረጠ ሁለት ሳምንት ያስቆጠረው ኤምባሲው፣ ንብረቶቹም ቤልጂየም ብራሰልስ ወደሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተዘዋውሯል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img