Friday, October 18, 2024
spot_img

ሕወሓት የእርዳታ መጋዘኖችን እየዘረፈ እንደሚገኝ የዩኤስኤአይዲ የኢትዮጵያ ሚሽን ዳይሬክተር ተናገሩ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ነሐሴ 26፣ 2013 ― ሕወሓት የእርዳታ መጋዘኖችን እየዘረፈ እንደሚገኝ የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅት (ዩኤስኤአይዲ) የኢትዮጵያ ሚሽን ዳይሬክተር ሺያን ጆንስ ከብሔራዊ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል፡፡

እንደ ዳይሬክተሩ ከሆነ የሕወሓት ወታደሮች በተለይ በገቡባቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች ሁሉ የእርዳታ መጋዘኖችን እንዲሁም እርዳታ የጫኑ ተሸከርካሪዎችንም ጭምር ዘርፈዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም እግራቸው በረገጠበት መንደር ሁሉ ከባድ ውድመት አድርሰዋል፡፡

የዩኤስኤአይዲ የኢትዮጵያ ሚሽን ዳይሬክተሩ ይህ መደረጉ ለተጎጂዎቹም ሆነ ለረጂዎቹ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

ዳይሬክተሩ አክለውም ሕወሃት ሁኔታውን ያለአግባብ እየተጠቀመበት እንደሆነ እናምናለን ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

እርዳታ በመዝረፍ በአሜሪካ ዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅት የተወነጀለው ሕወሓት በጉዳዩ ላይ እስካሁን የሠጠው ምላሽ የለም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img