Friday, October 18, 2024
spot_img

ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ ውስጥ በአስር ሺሕዎች ደብዛቸው መጥፋቱን ቀይ መስቀል አሳወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ነሐሴ 25፣ 2013 ― በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላው አፍሪካ ከ44 ሺህ በላይ ሰዎች እንደጠፉ መረጋገጡን የዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ (አይሲአርሲ) ዓለም አቀፉን የመጥፋት ቀንን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ቀይ መስቀል ጠፍተዋል ካላቸው መካከል 45 በመቶ የሚሆኑት ህፃናት ናቸው ብሏል።

ከነዚህ ከጠፉት 82 በመቶ ያህሉ በግጭት ከሚናጡ ከተባሉ ሰባት አገራት ብቻ መሆናቸውን ድርጅቱ አስታውቋል።

በአፍሪካ ውስጥ ከጠፉት ሰዎች ጠቅላላ ቁጥር ከግማሽ በላይ ናይጄሪያውያን ናቸው የተባለ ሲሆን፣ በአገሪቱ ውስጥ ወደ 24 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች መጥፋታቸው ተመዝግቧል።

በርካቶች የጠፉ ሰዎች ቁጥር የተመዘገበባቸው ሌሎች አገራት ደግሞ የኛዋ ኢትዮጵያ፣ ጎረቤት ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ሊቢያ፣ ዲሞክራቲክ ኮንጎ እና ካሜሩን ይገኙበታል።

በኢትዮጵያ ከ3 ሺህ 300 በላይ ሰዎች ጠፍተዋል በሚል መመዝገቡን የገለጸው ቀይ መስቀል፣
ከነዚህ ውስጥ 64 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች እና ሕፃናት ናቸው ብሏል፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ ደብዛቸው ጠፍቷል የተባሉት በርካታዎቹ ምክንያት ግጭትና ስደት ጋር የተያያዘ እንደሆነም ድርጅቱ አስታውቋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img