Wednesday, October 9, 2024
spot_img

በደቡብ አፍሪካ አዲስ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ተገኘ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ነሐሴ 25፣ 2013 ― በደቡብ አፍሪካ አዲስ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ መገኘቱን ተከትሎ ተመራማሪዎች በቅርበት እየተከታተሉት ነው ተብሏል።

በተደጋጋሚ የመለዋወጥ ባህርይ ያሳያል የተባለውና ሲ12 የተባለው ይህ ዝርያ እስካሁን ድረስ ባለው ስለ አስጊነቱ አልተገለጸም። በዚህ ዝርያ ተያዙ የተባሉ ሰዎች በመላው ደቡብ አፍሪካ ግዛቶች፣ በሰባት አፍሪካ አገራት፣ በእስያ፣ በአውሮፓና በኦሺኒያ መመዝገቡ ተገልጿል።

ሳይንቲስቶች ይህ ዝርያ ለኮሮናቫይረስ ‘አንቲ ቦዲስ’ ምን አይነት ባህርይ እንዳለውም እየተጠና ነው። ከዚህ በተጨማሪ ዝርያው ያለው የተለዋዋጭነት ባህርይ እንዲሁም ስለ ስርጭቱም ሌሎች ጥናቶች እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።

በዓለም ጤና ድርጅት የኮቪድ -19 የቴክኒክ መሪ የሆኑት ማሪያ ቫን ከርክሆቭ እንደሚሉት ዝርያው እስካሁን ባለው “በስርጭቱ ከፍ ያለ አይመስልም” ብለዋል። በአሁኑ ወቅት የዴልታ ዝርያ የዋነኝነቱን ስፍራ የያዘ ሲሆን ይህ ሁኔታ ከተለወጠ የዓለም የጤና ድርጅት ለህዝቡ ያሳውቃል ብለዋል።

ደቡብ አፍሪካ በከፍተኛ ሁኔታ በሚተላለፉት የዴልታ እና ቤታ የኮሮና ቫይረስ ዝርያዎች በወረርሽኙ ክፉኛ ተመትታለች። አገሪቱ 2,770,575 የኮሮና ቫይረስ ህሙማንን የመዘገበች ሲሆን፣ ከነዚህም ውስጥ 81,830 ህይወታቸውን አጥተዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img