Thursday, October 17, 2024
spot_img

በጉጂ ኦሮሞ፣ በአማሮ እና ቡርጂ ልዩ ወረዳ አከባቢዎች ሰላም ለማውረድ ሥምምነት ተደረሰ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ነሐሴ 25፣ 2013 ― በኦሮሚያ ክልል ምእራብ ጉጂ ዞን እንዲሁም በደቡብ ክልል አማሮ እና ቡርጂ ልዩ ወረዳ አከባቢዎች በተደጋጋሚ ሲፈፀሙ በቆዩ ጥቃቶች ሰላም ለማውረድ ከስምምነት ተደርሷል፡፡

በአዋሳ ከተማ በተካሄደውና የሁሉም ተወካዮች፣ የሃገር ሸማግሌዎች፣ የኃይማኖት አባቶች እና የጎሳ መሪዎች ባደረጉት ምክክር በባህላዊ መንገድ ሰላም ለማውረድ መስማማታቸውን ሸማግሌዎቹ መናገራቸውን የአሜሪካ ድምጽ ዘገባ ያመለክታል፡፡

በዚህ ስምምነት ላይ በሕዝብ መካከል የተፈጠረውን ስጋትና ጥርጣሬ ቀርፎ ሰላም ያወርዳል የተባለ ስምምነት ተፈጽሟል፡፡

በውይይቱ ላይ በሽማግሌዎቹ እና የአገር ሽማግሌዎቹ ዘንድ በማህበረሰብ ውስጥ ተሸሽጎ ጥቃት ያደርሳል በሚል በመንግስት ኦነግ ሸኔ የሚባለውና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ሲል የሚጠራው ቡድን ስሙ ተጠቅሷል፡፡

በተካሄደው መድረክ ከስምምነት የተደረሱ ስምምነቶችን ለማስፈጸም የኦሮሚያ እና የደቡብ ክልል የፀጥታ አካላት እና የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ሂደቱን ያመቻቻሉ ተብሏል።

በአማሮ ልዩ ወረዳና በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን አዋሳኝ ቦታዎች ባለፉት ዓመታት በተደጋጋሚ ሲከሰት ለነበረው ግጭት መቋጫ ለማበጀት በማሰብ ከዚህ ቀደም ተደጋጋሚ ሙከራዎች ሲደረጉ ሰንብቷል፡፡ ከወራት በፊት በሁለቱ አካባቢዎች አዋሳኝ ቦታ ላይ በምትገኘው ዳኖ ቀበሌ ላይ እየተካሄደ በነበረ ስብሰባ ሳይቀር ታጣቂዊች አድርሰውታል በተባለ ጥቃት የሰዎች ሕይወት ተቀጥፏል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img