Thursday, October 17, 2024
spot_img

በሰሜን የአገሪቱ ክፍል ባለው ጦርነት ሰበብ ከ7 ሺሕ በላይ ት/ቤቶች ወድመዋል ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ነሐሴ 24፣ 2013 ― በጥቅምት ወር የመጨረሻ ሳምንት በትግራይ ክልል ተጀምሮ በቅርብ ሳምንታት ወደ አፋር እና አማራ ክልሎች በተስፋፋው ጦርነት ሰበብ ከ7 ሺሕ በላይ ትምህርት ቤቶች መውደማቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ ገልጸዋል፡፡

በጦርነቱ ከወደሙት ትምህርት ቤቶች መካከል በርካቶቹ ሙሉ ለሙሉ መውደማቸውንም ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

ይህንኑ የትምህርት ቤቶቹን ውድመት ተከትሎም በተለይ በትግራይ ክልል ከ1 ነጥብ 4 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፣ በአፋር እና አማራ ክልሎችም በተመሳሳይ ከትምህርት ገበታ ውጪ የሚሆኑ ትማሪዎች ስለመኖራቸውም ተጠቅሷል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img