Sunday, October 6, 2024
spot_img

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሀገር አቀፍ የጸሎት ጥሪ አስተላለፈች

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ነሐሴ 24፣ 2013 ― የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ምእመናን በወርሐ ጳጉሜ ስለ ሀገር ሰላም በልዩ ሁኔታ ጸሎት እንዲያደርጉ ጥሪ አስተላልፋለች።

የጸሎት ጥሪው የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ያስተላለፈውን ዓለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ የጸሎት ጥሪ ተግባራዊ ለማድረግ ታልሞ የተላለፈ መሆኑ ተገልጿል።

በጥሪው በተለይ ጳጉሜ አንድ ቀን ሥራ ዝግ ሆኖ ምእመናን በየቁምስናዎቻቸው የሰላም ጸሎት እንዲያደርጉ አደራ ጭምር ተጠይቋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በዕለቱ የሚሰበሰቡ የዓይነትም ሆነ የገንዘብ መባዕ በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በየመጠለያ ጣብያው ለሚገኙ ወገኖች የሚሰራጭ መሆኑን ቤተክርስቲያኗ ያስታወቀች ሲሆን፣ ምእመናን ይህንኑ ተገንዝበው ንቁ ትብብር እንዲያደርጉ ተጠይቋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘም ጊዜው የኮቪድ 19 ስርጭት ያገረሸበት በመሆኑ በጋራ የሚከናወኑ መርሃ ግብሮች በሙሉ የጥንቃቄ መመሪያዎችን የተከተሉ መሆናቸውን ክቡራን ቆሞሳት እና የሚመለከታቸው አካላት እንዲያረጋግጡ ጥሪ መተላለፉን ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የተገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img