Wednesday, October 9, 2024
spot_img

ባለሥልጣኑ ባስቀመጠው መመሪያ የማይመዘገቡ የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃንን እንደሚዘጋ አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ነሐሴ 24፣ 2013 ― የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ባጸደቀው የምዝገባ ውሳኔ መሠረት የማይመዘገቡ የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃን ተቋማትን እንደሚዘጋ አስታውቋል፡፡

የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር አበራ ወንድወሰን በቅርቡ የጸደቀውን ሕግ የሚያከብሩን የማስተናገድ ኃላፊነትና ግዴታ ባለሥልጣኑ እንዳለበት ሁሉ ምዝገባውን ለማይፈጽሙ የሚዲያ ተቋማት፣ የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣኑ የመዝጋት ሥልጣን እንዳለው ተናግረዋል።

ዳይሬክተሩ እንደተናገሩት ከሆነ፣ ማንኛውም በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ተቋም ዝርዝር ውስጥ ያልተካተተ ሚዲያ ከመንግሥት ምንም አይነት ሥራውን ለማከናውን የሚያስችል ሕጋዊ እውቅናም ሆነ ጥቅማ ጥቅም ሊያገኝ አይችልም መባሉን ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ ገልጸዋል፡፡

በምዝገባው ተሳትፎ እውቅና ያልተሰጠው የትኛውም የሚዲያ ተቋም ጥቃትና ኪሳራ ቢደርስበት ችግሩን ራሱ እንደሚወስድና መንግሥት ከለላ እንደማያደርግ እንዲሁም ተጠያቂነትም እንደማይኖረውም ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ወቅትም ምዝገባው እያካሄደ ይገኛል የተባለው ባለስልጣኑ፣ ከሰላሳ አምስት በላይ የሚሆኑ ታዋቂ ሚዲያዎችን በምዝገባው አሳትፏል የተባለ ሲሆን፣ እስካሁን ምዝገባውን ቢፈጽሙም፣ የአገር ሉዓላዊነትን የሚጥስ መረጃን ከማስተላለፍ ያልተቆጠቡ ተቋማት ስላሉ የወጣውን ሕግ አግባብነት ተረድተው እንዲያስተካክሉም እንደተነገራቸው ነው የተገለጸው።

እያንያንዱ የሚዲያ ተቋም የሚሠራው ሥራ በየቀኑ ሪፖርት እየተደረገለት መሆኑን የጠቆሙት ም/ዋና ዳይሬክተሩ፣ የሚዲያ ተቋማት አገሪቱ ያለችበትን ሁኔታና የአገሪቱን ዲፕሎማሲ እንዲረዱ የማሳሰቢያ ጊዜ ቢሰጥም፣ ከተለመደው አሠራር ካልተገደቡ ይዘጋሉ ብለዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img