Sunday, September 22, 2024
spot_img

የሕዳሴ ግድብ ዘንድሮ በሱዳን የጎርፍ መጠን ላይ ተጽዕኖ አላሳደረም ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ነሐሴ 24፣ 2013 ― የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ በዚህ ዓመት በሱዳን የተከሰተው የጎርፍ መጠን ላይ ምንም ተጽዕኖ እንዳላሳደረ ተነግሯል፡፡

የሱዳን የመስኖ ሚንስትር ያሲር አባስን ጠቅሶ ሬውተርስ የዜና ወኪል እንደዘገበው፣ በዚህ ዓመት በሱዳን በተከሰተው የጎርፍ መጠን ላይ የሕዳሴ ግድቡ ምንም ለውጥ አላስከተለም።

ሱዳን በግድቡ ምክንያት የጎርፍ መጠን ለውጥ ያመጣል በሚል ስጋት ከፍተኛ ወጪ አውጥታ ቅድመ ጥንቃቄ ስታደርግ እንደነበርም ተዘግቧል።

የሱዳን የመስኖ ሚንስትር ያሲር አባስ በትዊተር ገጻቸው ‹‹ግድቡ ውሃ ቢሞላም የግድቡ ግንባታ በዚህ ዓመት የጎርፍ መጠን ላይ ተጽዕኖ አላሳደረም። ነገር ግን ከውሃ ሙሌቱ በፊት የመረጃ ልውውጥ ስላልነበረ ሱዳን ጎርፍ በምጣኔ ሀብቷ እና በማኅበራዊ ሕይወት የሚፈጥረውን ተጽዕኖ ለመቅረፍ ስትል ለቅድመ ጥንቃቄ ከፍተኛ ወጪ አውጥታለች›› ብለዋል።

በቅርቡ ኢትዮጵያ ለሁለተኛ ዙር የታላቁን ሕዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት ስታከናውን ግብፅ እና ሱዳን መቃወማቸው አይዘነጋም።

ከአምስት ሺህ ሜጋ ዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫል ተብሎ የሚጠበቀው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ሲተናቀቅ ከአፍሪካ ግዙፉ የኤሌክትሪክ ማመንጫ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

ግንባታው ከሰማንያ በመቶ በላይ የተጠናቀቀው ግድብ በቅርቡ የሙከራ ኃይል ማመንጨት ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡

ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ከፍተኛ መጠን ያለው የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት ለአካባቢው አገራት ከማቅረቡ በተጨማሪ፤ በየዓመቱ በጎርፍ የምትጠቃውን የሱዳንን ጫና ይቀንሰዋል ተብሏል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img