Sunday, September 22, 2024
spot_img

የጸጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ በዝግ መከረ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ነሐሴ 21፣ 2013 ― የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምር ቤት በትግራይ ክልል ግጭት ዙሪያ ውይይት አድርጓል።

በውይይቱ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬስ የተገኙ ሲሆን፤ በጦርነቱ የተካፈሉ አካላት በሙሉ የተኩስ አቁም እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

ምንም እንኳን የኢትዮጵያ መንግስት የተናጥል ተኩስ አቁም በማወጅ ከትግራይ ክልል ቢወጣም የህወሓት ሀይሎች ወደ ጎረቤት አፋር እና አማራ ክልሎች ጥቃት በመክፈታቸው አጠቃላይ የተኩስ አቁም ላይ መደረስ እንደልተቻለም ገልጸዋል።

ከወራት በፊት በትግራይ ክልል የተከሰተው ግጭት አሁን ላይ እየተስፋፋ መሆኑን እና በርካታ ሰብአዊ ኪሳራዎች እያስከተለ መሆኑን ተናግረዋል። በጦርነቱ ሳቢያ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በየእለቱ እያሻቀበ መሆኑን እና ከ2 ሚሊየን በላይ ኢትዮጵያውያን ግጭቱን ተከትሎ መፈናቀላቸውን አስታውቀዋል።

ከትግራይ ክልል በተጨማሪም ወደ አማራ እና አፋር ክልል በተስፋፋው ግጭት ከ300 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውንም አስታውቀዋል። ግጭቱ ከሰብአዊ ቀውስ በተጨማሪም የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ክፉኛ እየጎዳ ነው ያሉት ጉቴሬስ፤ የበሀገሪቱ የብድር ጣራ እየጨመ ነው፤ እዳ የመክፈል አቅሟ እየተዳከመ መጥቷል፣ የኑሮ ውድነቱም በከፍተኛ ሁኔታ እያሸቀበ ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ አንድነት እና የቀጠናው መረጋጋት ወሰሳኝ ናቸው ያሉት ጉቴሬስ፤ አሁን ላለው ሁኔታ ወታደራዊ መፍትሄ የለም ሲሉም ተናረዋል። በጦርነቱ የተካፈሉ አካት በሙሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የተኩስ አቁም እንዲያድርጉ፣ የውጭ ሀገራት ሀይሎች ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ፣ ለሰብአዊ ድጋች መተላለፊያ መንገዶች እንዲከፈቱ እና ችግሩን ለመቅረፍ በኢትዮጵያ የሚመራ እና ሁሉንም አካታች የሆነ ውይይት እንዲካሄድ ጥሪ አቅርበዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኢትዮጵያ ውይይት እንዲጀመር ከአፍሪካ ህብረት እና ከሌሎች ሀገራ ጋር ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ዋና ጸሃፊው አስታውቀዋል።

የፈረንሳይ እና አየርላንድ ተወካዮች በበኩላቸው በትግራይ ክልል የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ የተፈጠሩ ነገሮች አሳሳቢ ናቸው ያሉ ሲሆን፤ የህወሓት ሀይሎች በአስቸኳይ ከወረሩት የአፋር እና የአማራ ክልል ለቀው እንዲወጡ፤ የአማራ ክልል ሀይሎች ከያዙት የትግራይ ክልል መሬት እንዲለቁ እንዲሁም ሁሉን አካታች የሆነ ውይይት እንዲጀመር ጥሪ አቅርበዋል።

የአሜሪካ ተወካይ በበኩላቸው፤ በአፋጣኝ ተኩስ አቁም እንዲደረግ፣ ያልተገደበ የሰብአዊ ድጋፍ መስመር እንዲከፈት እና ሁሉንም ኢትዮጵያውያን ያካተተ ውይይት እንዲጀመር አሜሪካ ጥሪ አቅርባ ነበር እስካሁን የተጀመረ ነገር የለም፤ በኢትዮጵያ መንግስተ በኩልም በጎ ምላሽ አላገኘንም ብለዋል።

የቻይና ተወካይ በበኩላቸው በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ ሁሉም አካላት በራሳቸውመ መንግድ በሚያድርጉት የፖለቲካ ውይይት ልዩነቶቻቸውን እንደሚፈቱ ቻይና ታምናለች ብለዋል። በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ የሰብአዊ ድጋፍ ሰጪ ድርጅቶች ስራቸውን በሚሰሩበት ጊዜ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ባከበረ መልኩ መሆን ይገባል ያሉት ተወካዩ፤ ለኢትዮጵያ የሚደረገው የሰብአዊ ድጋፍም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

በሰብአዊ መብት እና በሰብዓዊ ድጋፍ ስም በኢትዮጵየ የውስጥ ጉዳይ ላይ የሚደረጉ ጣልቃ ገብነቶችን ቻይና አጥብቃ ትቃወማለችም ብለዋል። የኬንያ እና የህንድ ተወካዮችም የትግራይ ክልል ግጭት መፍትሄ በኢትዮጵየውያን መሪነት መምጣት አለበት የሚል ሀሳብ አንስተዋል።

በተመድ የኢትዮጵያ ቋሚ መልእክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ፤ የህወሓትን ጸብ አጫሪነት ለምክር ቤቱ ያብራሩ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ መንግሰት ባሳለፍነው ሰኔ ወር ላይ ተኩስ አቁም አውጆ መውጣቱ በአካባቢው ለሰብአዊ እንቅቃሴ እንዲሁም ሰላም እና መረጋጋትን ለማምጣት ነበር ብለዋል። ሆኖም ግን የህወሓት ሀይሎች ወደ ተኩስ አቁም የመምጣት ፍላጎት የላቸውም፤ ይባስ ብሎም ህጻናትን ወደ ውትድርና እያስገቡ ነው፤ ወላጆች ልጆቻውን ለውትድርና እንዲሰጡ እርዳታ እህልን እንደ ማስፈራሪያ እየተጠቀሙ ነው ብለዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img