Sunday, September 22, 2024
spot_img

የሕዳሴ ግድብን አስመልክቶ ቱኒዚያ ለፀጥታው ምክር ቤት ያቀረበችው ረቂቅ የውሳኔ ሐሳብ ውድቅ እንዲደረግ ኢትዮጵያ ጠየቀች

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ነሐሴ 21፣ 2013 ― የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት አባል ሀገራት አምባሳደሮችን አነጋግረዋል።

አቶ ደመቀ መኮንን በዚሁ ወቅት፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን አስመልክቶ በቱኒዚያ አማካይነት የቀረበው ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ውድቅ እንዲደረግ ወቅት ጥሪ ማቅረባቸውን አል ዐይን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰምቻለሁ ብሎ ዘግቧል፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን በዚሁ ወቅት ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት አስተባባሪነት የሚካሄደው የሶስትዮሽ ድርድርን በማስቀጠል ከስምምነት ላይ እንዲደረስ ቁርጠኛ መሆኗንም ማስገንዘቧ የተነገረ ሲሆን፣
በቱኒዚያ የቀረበው ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ምክር ቤቱ እንዳያሳልፈው አምባሳደሮቹ ለየሀገሮቻቸው መልዕክቱን እንዲያስተላልፉ ጠይቀዋል።

የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ስለሺ በቀለ በበኩላቸው የአባይን ውሃ አጠቃላይ መረጃ፣ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን የግንባታ ደረጃ እና የግድቡ ጠቀሜታን፤ በቱኒዚያ አማካይነት ለተ.መ.ድ የጸጥታው ምክር ቤት የቀረበውን ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ይዘት በተመለከተ እንዲሁም በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያን አቋምን አስመልክቶ ለአምባሳደሮቹ ገለጻ ሰጥተዋል።

ዶ/ር ስለሺ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን የልማት ፕሮጀክት በመሆኑ በጸጥታው ምክር ቤት መታየት የሌለበት ጉዳይ መሆኑን ጠቁመዋል።

አያያዘውም ከዚህ በሐምሌ ወር ጉዳዩ ለጸጥታው ምክር ቤት ቀርቦ፤ ሶስቱ ሀገራት በአፍሪካ ህብረት አስተባባሪነት የሚካሄደውን የሶትስትዮሽ ድርድር በማስቀጠል መፍትሔ ላይ እንዲደርሱ አቅጣጫ መቀመጡን አስታውሰዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img