አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ነሐሴ 20፣ 2013 ― የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያንይ ዪ ጋር በስልክ ተወያይተዋል።
በአቶ ደመቀ መኮንን ጥያቄ አቅራቢነት ተካሄዷል በተባለው በዚህ ውይይት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ቻይና ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስን ለመዋጋት በምታደርገው ጥረት ለምታደርገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋውበታል ተብሏል፡፡
ኢትዮጵያም የኢትዮ ቻይናን ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂክ የትብብር አጋርነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል።
አያይዘውም ኢትዮጵያም እንደ ቻይና ምዕራባውያን በሰብአዊ መብት ስም በሌሎች ሃገራት የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት አጥብቃ እንደምታቃወም ጠቅሰዋል።
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒትር በበኩላቸው ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን እና ነጻነቷን ለማስጠበቅ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ የሃገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያን ዪ ማስታወቃቸውን የአገሪቱ የውች ጉዳይ መስሪያ ቤት አመልክቷል፡፡
አያይዘውም የኢትዮጵያ መንግስት የውስጥ ጉዳዮቹን በአግባቡ መያዝ የሚችልበት አቅም አለው ብለው እንደሚያምኑም ገልጸዋል ነው የተባለው፡፡
የሁለቱ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ውይይት በዛሬው እለት በትግራይ ጉዳይ በዝግ ይካሄዳል ከተባለው የተመድ የጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ጉባኤ በፊት የተደረገ ነው፡፡