Sunday, September 22, 2024
spot_img

የሲዳማ ብሔራዊ ነጻነት ግንባር እነ ሕወሓትን ለመቀላቀል መወሰኑን አሳወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ነሐሴ 19፣ 2013 ― የሲዳማ ብሔራዊ ነጻነት ግንባር ሕወሓት እና በመንግስት ኦነግ ሸኔ የሚባለውንና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ሲል የሚጠራውን ቡድን ለመቀላቀል መወሰኑን አሳውቋል፡፡

ግንባሩ ይህንኑ ባሳወቀበት መግለጫው ኢትዮጵያ ገብታበታለች ላለው ውድቀት መንግስት እና ገዢው ብልጽግና ፓርቲ ይከተሉታል ያለውን ‹‹የተሳሳተ›› ሲል የጠራውን የፖለቲካ ርእዮተ ዓለም ተችቷል፡፡

የሲዳማ ብሔራዊ ነጻነት ግንባር ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የመበታተን አደጋ ተጋርጦባታል ያለ ሲሆን፣ የብሔረሰቦችን መብት አሀዳዊ ካለው አስተሳሰብ ለመጠበቅና አገሪቱንም ከመበታተን ለመታደግ ሕወሓት እና በመንግስት ኦነግ ሸኔ የሚባለውንና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ሲል የሚጠራውን ቡድን ለመቀላቀል መወሰኑን ነው ያሳወቀው፡፡

በመግለጫው የፌዴራሊስት ኃይሎችን ባንድነት መቆም የጠየቀው የሲዳማ ብሔራዊ ነጻነት ግንባር፣ አሁን ያለው የኢትዮጵያ ችግር የሚፈታውም ሁሉንም ያካተተ የሽግግር መንግስት በበመስረት የሕግ የበላይነትን በማስከበር እና የሕዝቦችን ራስን በራስ የማስተዳደር መብት በማክበር ነው ብሏል፡፡

አሁን የሲዳማ ብሔራዊ ነጻነት ግንባር ተቀላቅያቸዋለሁ ያላቸው ከፌዴራል መንግስት ጋር ጦርነት ውስጥ የሚገኘው ሕወሃት እና በመንግስት ኦነግ ሸኔ የሚባለውንና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ሲል የሚጠራውን ቡድን ከቀናት በፊት በተመሳሳይ አብረው ለመስራት ተስማምተናል ማለታቸው ይታወሳል፡፡

ጥምረቱን በተመለከተ መግለጫው የሰጠው የፌዴራል መንግስቱ፣ ቡድኖቹ ከዚህ ቀደም በአገሪቱ የተለያዩ አካበቢዎች ለሚደርሱ የንጹሐን ጥቃቶች ተጠያቂ መሆናቸውንና አዲስ አነገር እንዳልሆነ አሳውቋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img