Monday, November 25, 2024
spot_img

መንግሥት ኤምባሲዎች እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የጥበቃ ሠራተኞቻቸውን ማንነት እና ብሔር እንዲያሳውቁ መጠየቁን ሾልኮ ወጣ የተባለ የአውሮፓ ኅብረት ሰነድ አመለከተ

– ሰነዱ በተጨማሪ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ከቱርክ እንዲመጣ ፈልገዋል ያለውን ድሮን አመልክቷል

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ነሐሴ 18፣ 2013 ― መንግሥት መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ ሁሉም የውጭ አገራት ኤምባሲዎችና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ማንነት እና ብሔርን ጨምሮ የጥበቃ ሠራተኞቻቸውን ዝርዝር መረጃ እንዲያሳውቁ መጠየቁን ሾልኮ ወጣ የተባለ የአውሮፓ ኅብረት ሰነድ አመልክቷል፡፡

መረጃውን እንዲያሳውቁ ከተጠየቁት መካከል በርካታ የአውሮፓ አገራት ኤምባሲዎች ይህን ለመፈጸም እቅድ እንደሌላቸው በሰነዱ ላይ ሰፍሯል፡፡

ሰነዱ ይህንኑ ትእዛዝ ለኤምባሲዎቹና ለዓለም አቀፍ ድርጅቶች አስተላልፏል ያለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ሲሆን፣ ትእዛዙ በቃል የተላለፈ ስለመሆኑም ነው የተገለጸው፡፡

የአውሮፓ ኅብረት በጉዳዩ ላይ የያዘው አቋም ይፋ ያልተደረገ ሲሆን፣ ይኸው ጉዳይ በዛሬው እለት ይካሄዳል በተባለ ስብሰባ አቅጣጫ ይሰጥበታል ተብሏል፡፡

በሌላ በኩል ይኸው ሾልኮ ወጥቷል የተባለ ሰነድ በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቱርክ ያደረጉትን ጉብኝት ያነሳ ሲሆን፣ ቱርክ በወታደራዊ ቴክኖሎጂ እና የድሮን ድጋፍ እንድታደርግ ጠይቀዋል ብሏል፡፡

እንደ ሰነዱ ከሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተለይ ፍላጎት ያሳዩት Bayraktar-TB2 እና ANKA-S በተባሉ ወታደራዊ ቴክኖሎጂዎች መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img