Thursday, October 17, 2024
spot_img

ዩኤስኤአይዲ ለታጣቂዎች የምግብ ርዳታ ይደረጋል የሚለውን ክስ አንደማይቀበለው አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ነሐሴ 18፣ 2013 ― የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤአይዲ) በተቋሙ እውቅና ለታጣቂዎች የምግብ ርዳታ እንደሚሰጥ ተደርጎ የቀረበውን ክስ አንደማይቀበል በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ በትዊተር ገጹ ላይ አስፍሯል፡፡

ኤምባሲው ዛሬ ባስነበበው ማስታወሻ እንደገለጸው ከሆነ የረድኤት ድርጅቱ በምግብ እደላ ወቅት ምግብ ለታጣቂዎች ሳይሆን፣ ርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች በትክክክል መድረሱን የሚከታተል መሆኑን የጠቆመ ሲሆን፣ ነገር ግን እንዲህ ባለው የግጭት ወቅት ታጣቂዎች ለተረጂዎች የሚቀርቡ ምግቦችን ሊዘርፉ የሚችሉበት እድል ሰፊ ነዉ ብሏል፡፡

የኤምባሲው ማስተባበያ የመጣው በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ባለው ግጭት ውጊያ ላይ የነበሩ የጦር መሪ በመከላከያ ኃይሎች ተማርከዉ በቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅት የረድኤት ድርጅቱ ሥም የታተመበት አልሚ ምግብ ይዘዉ አንደተገኙ ለመንግስት ቅርበት ባላቸው መገናኛ ብዙኃን በመዘገቡ ነው፡፡

ዩኤስኤአይዲ የሕይወት አድን ምግብ እና አንክብካቤ በማድረግ በኩል ትልቁ የኢትዮጵያ ለጋሽ አንደሆነ የጠቀሰው ኤምባሲው፣ በአሁኑ ሰዓት በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች 7 በመቶ ለሚሆኑ የኢትዮጵያን ዜጎች ርዳታ እያቀረበ እንደሚገኝም ገልጿል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img