Thursday, October 17, 2024
spot_img

የጸጥታ ጥበቃው ምክር ቤት በመጪው ሐሙስ በትግራይ ጉዳይ እንደሚመክር ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ነሐሴ 18፣ 2013 ― የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታ ጥበቃው ምክር ቤት፤ በኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ባለው ነባራዊ ሁኔታ ላይ በመጪው ሐሙስ በዝግ ሊመክር መሆኑ ተሰምቷል፡፡ ምክር ቤቱ በትግራይ ክልል ውጊያ ከተቀሰቀሰ ወዲህ በጉዳዩ ላይ ሲወያይ የሐሙሱ ለስምንተኛ ጊዜ ነው።

የትግራይ ሁኔታን በተመለከተ የጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ እንዲያደርግ የጠየቁት ስድስት ሀገራት መሆናቸው የተነገረው ሲሆን፣ እነዚህ አገራት አየርላንድ፣ ኢስቶኒያ፣ ፈረንሳይ፣ ኖርዌይ፣ ብሪታኒያ እና አሜሪካ ናቸው፡፡

ስድስቱ ሀገራት ስብሰባው እንዲካሄድ የጠየቁት፤ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በኢትዮጵያ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ ማቅረባቸውን ተከትሎ ስለመሆኑም ተዘግቧል፡፡

ጉተሬዝ በሐሙሱ ስብሰባ ላይ ተገኝተው በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁ የዲፕሎማቲክ ምንጮች ነግረውኛል ብሎ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረ ገጽ ጽፏል፡፡

ከተመድ ዋና ጸሐፊ በተጨማሪ በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ በተጓዙበት ወቅት ትግራይን ጎብኝተው የተመለሱት የድርጅቱ የሰብዓዊ እና የአስቸኳይ እርዳታ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፊትዝም በስብሰባው ላይ እንደሚሳተፉ ነው የተነገረው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img