Monday, September 23, 2024
spot_img

ኤርትራ በጦር መሪዋ ላይ አሜሪካ የጣለችውን ማዕቀብ ውድቅ አደረገች

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ነሐሴ 18፣ 2013 ― ኤርትራ ከትግራይ ጦርነት ጋር በተገናኘ በጦር መሪዋ ጄነራል ፊሊጶስ ወልደዮሐንስ ላይ በአሜሪካ የጣለችውን ማዕቀብ መሠረተ ቢስ ነው ብላዋለች፡፡

ኤርትራ መሠረተ ቢስ ያለችውን የአሜሪካን የማዕቀብ እርምጃ በተመለከተ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ በኩል መግለጫ አውጥታለች።

የአሜሪካ አስተዳደር በጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል ፊሊጶስ ወልደዮሐንስ ላይ ተቀባይነት የሌላቸውን ክሶች ሰንዝሯል ያለው መግለጫው፣ የኤርትራ መንግስት የተቃጣበትን መሠረተ ቢስ ውንጀላ እና ክስ በደብዳቤም ሆነ በመንፈስ እንደማይቀበል አስታውቋል።

የአሜሪካ አስተዳደር እንዲህ ዐይነት መሠረተ ቢስ የውንጀላ ዘመቻዎችን በኤርትራ ላይ ሲያደርግ የመጀመሪያው እንዳልሆነም ለአገሪቱ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ኃላፊ አንቶንዮ ብሊንክን የተሰጠውን መልስ አስታውሷል፡፡

ኤርትራ ምክንያታዊ ያልሆኑ ያለቻቸው ተደጋጋሚ ክሶችን በዝምታ ልታልፍ እንደማትችልም መግለጫው ይጠቁማል።

ሐሰተኛ ያለው ውንጀላ ሊጣራ የሚችል ነገር ካለው በገለልተኛ አካል እንዲጣራም ለአሜሪካ አስተዳደር ጥሪ አቅርቧል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ተደጋጋሚ የዓለም አቀፍ ህግጋትና የሃገራትን የሉዓላዊነት ጥሰቶች በመግታት እና መፈትሔ በመፈለግ ረገድ ኃላፊነቱን እንዲወጣም አሳስቧል።

በትግራይ ጦርነት የሚመሩት ጦር የተለያዩ ሰብዓዊ ጥሰቶችንና ግድያዎችን ፈጽሟል ያለው የአሜሪካ ፌዴራል ግምጃ ቤት፣ ጄነራል ፊሊጶስ በአሜሪካ አላቸው ያለውን ሐብት እንዳያንቀሳቅሱ ማገዱን ማስታወቁ የሚታወስ ነው።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img