Sunday, September 22, 2024
spot_img

አሜሪካ ከትግራይ ጦርነት ጋር በተገናኘ በኤርትራ የጦር አዛዥ ጀነራል ፊሊጶስ ወልደዮሐንስ ላይ ማዕቀብ ጣለች

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ነሐሴ 17፣ 2013 ― አሜሪካ የኤርትራ ጦር በትግራይ ክልል ፈጽሟል ባለችው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ምክንያት በጦሩ ዋና አዛዥ ጄነራል ፊሊጶስ ወልደዮሐንስ ላይ ማዕቀብ መጣሏን አስታውቃለች።

ማዕቀቡን የተጣለው በአሜሪካ የፌዴራል ግምጃ ቤት (ትሬዠሪ) በኩል ሲሆን፣ አዛዡ በአሜሪካ ያላቸው ሐብት እንዲታገድ እንደተወሰነ ነው የተገለጸው።

አሜሪካ በጄነራል ፊሊጶስ ወልደዮሐንስ የሚመራው የኤርትራ ጦር በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን መፈጸሙን፣ ሴቶችን መድፈሩን እንዲሁም ወጣቶችን እና ንጹሀን ዜጎችን ቤት ለቤት በመዞር ገድሏል ስትል ከሳለች።

የኤርትራ ጦር የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት የተናጠል የተኩስ አቁም ካደረገ በኋላም ተመልሶ ወደ ትግራይ ክልል ገብቷል የሚለው የአሜሪካ ግምጃ ቤት፣ ጦሩ በአስቸኳይ ወደ ኤርትራ እንዲመለስ ጠይቋል።

ውሳኔው አሜሪካ ለሰብአዊ መብት ጥበቃ ያላትን ቁርጠኝነት ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚችልም ነው ግምጃ ቤቱ ያስታወቀው።

አሁንም ጦርነቱ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ነው ያለው ተቋሙ፣ በቀጠለው ግጭት ምክንያት እርዳታ የሰብአዊ መብት ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ማድረስ ባለመቻሉ ሁሉም አካላት ግጭቱን እንዲያስቆሙ ጠይቋል።

ኤርትራ ማዕቀቡን በተመለከተ እስካሁን የሰጠችው ምላሽ የለም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img