Thursday, October 17, 2024
spot_img

በትግራይ ክልል በኢንቨስትመንት የተሰማሩ የግብጽ ኩባንያዎች የኢትዮጵያ መንግስት ላይ ክስ መመስረታቸው ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ነሐሴ 17፣ 2013 ― በትግራይ ክልል መዋዕለ ንዋያችንን አፍስሰን የተሰማራንበት ኢንቨስትመንት በግጭቱ ምክንያት እየተደናቀፈብን ነው ያሉ የግብጽ ኩባንያዎች የኢትዮጵያ መንግስት ላይ ክስ መስርተዋል ሲል ኢጅብት ኢንዲፔንደንት ዘግቧል፡፡

በትግራይ ክልል ውስጥ ባለው የኢንዱስትሪ ዞን ላይ ጉዳት በመድረሱ እና ግጭቱ ከተጀመረ ጀምሮም ለአንድ ዓመት ተኩል ያህል ስራቸው በመስተጓጎሉ ምክንያት የግብፅ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ላይ ዓለም አቀፍ ክስ በይፋ መክፈታቸውን የጠቀሰው ዘገባው ካይሮ 24 የተባለ ድረ ገጽን ዋቢ አድርጎ አስነብቧል፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የግብፅ ኢንቨስትመንቶች ወደ 40 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ኪሳራ እንደደረሰባቸው ያመለከቱት የኢንዱስትሪ ዞኖቹ ኃላፊ አላ አል ሰቅጢ፣ ባለሐብቶቹ መብታቸውን ለማስከበር በኢትዮጵያ በተከሰቱ ግጭቶች የደረሰውን ኪሳራ ለማካካስ ወደ ዓለም አቀፉ ዳኝነት መሄዳቸውን ገልጸዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img