አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ነሐሴ 17፣ 2013 ― በሳዑዲ ዓረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰባቸው ያለውን እስር፣ ግፍ እና መከራ የሚያወግዝ የተቃውሞ ሰልፍ አዲስ አበባ በሚገኘው የሳዑዲ ኤምባሲ ተካሂዷል።
“እኔም ለወገኔ ድምፅ ነኝ” በሚል መሪ ቃል በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ፣ ሰልፈኞቹ በሳዑዲ በእስር በሚገኙ ሴቶች ሕፃናት እና ወጣቶች ላይ እየተፈጸመባቸው ያለው ግፍ እንዲቆም ጠይቀዋል።
ሳዑዲ በኢትዮጵያውያን ላይ እየፈጸመች ያለችው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት በማቆም በእስር ላይ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው እንድትመልስም ሰልፈኞቹ ጠይቀዋል።
በሳዑዲ በእስር ላይ 80 ሺህ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን እንደሚገኙ መረጃዎች እንደሚያሳዩ የኢቲቪ ዘገባ ያመለክታል፡፡