Thursday, October 17, 2024
spot_img

ሕወሓት የእንግሊዙ ቴሌግራፍ በአጋምሳ ጥቃት አድርሷል በሚል ያወጣውን የምርመራ ዘገባ ውድቅ አደረገ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ነሐሴ 14፣ 2013 ― በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀው የሕወሃት ኃይሎች በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ሰላማዊ ሕዝብ ላይ በፈጸሙት የበቀል ጥቃት ዓለም አቀፍ የጦር ወንጀል ፈጽመዋል በሚል የምርመራ ዘገባ ይዞ መውጣቱ ይታወሳል፡፡

ሆኖም በጉዳዩ ላይ መግለጫ ያወጣው ሕወሓት ዘገባውን ውድቅ ያደረገ ሲሆን፣ ጋዜጣው ዘገባውን እንዲያስተባብልም ጠይቋል። ሕወሓት ውንጀላው በጣት ከሚቆጠሩ ተፈናቃዮች በተሰበሰበ መረጃ ላይ ብቻ የተመሠረተ እና ተዓማኒነት የሌለው ነው ብሏል፡፡

‹‹አጋምሳ›› በተባለ መንደር በሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ ተፈጸመ የተባለው ግድያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እውቅና ባለው ገለልተኛ አጣሪ አካል እንዲጣራ እና በማጣራቱ ሂደትም የራሱ ኃይሎች ተባባሪ እንደሚሆኑ ሕወሃት በመግለጫው ጠይቋል።

ቴሌግራፍ ባወጣው ዘገባ የሕወሃት ተዋጊዎች በክልሉ በርካታ ሰላማዊ ሰዎችን ገድለው መኖሪያ ቤቶችን አቃጥለዋል ያለ ሲሆን፣ በጥቃቱ እስከ 100 የሚገመቱ ሰዎች ሳይገደሉ እንዳልቀሩ ተገምቷል፡፡

በትላንትናው እለት መግለጫ የሰጡት የጠቅላይ ሚኒትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪ ቢልለኔ ሥዩም፣ ሕወሃት በቅርቡ በአማራ እና በአፋር ክልሎች ጥቃት መፈጸሙን እና ሰርጎ በገባባቸው አካባቢዎች በከፍተኛ ደረጃ ሕዝብ ማሸበሩን፤ የግለሰቦችን ንብረት መዝረፉን፤ የሕክምና ተቋማትን ጨምሮ የመሰረተ ልማት አውታሮችን እያወደመ መቀጠሉን ተናግረዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img