Thursday, October 17, 2024
spot_img

62 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንና ሰራተኞች በህግ ተጠያቂ ሊደረጉ ነው

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ነሐሴ 14፣ 2013 ― ሐብትና የገቢ ምንጫቸውን ለማስመዝገብ ፈቃደኛ ያልሆኑ 62 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንና ሰራተኞች በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የፌደራል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

በኮሚሽኑ የፀረ-ሙስና ህግ ምክር፣ ትግበራና ልምድ ቅመራ ዳይሬክተር ገዛኸኝ ጋሻው እንደገለፁት ሀብትና የገቢ ምንጫቸውን ለማስመዝገብ ፈቃደኛ ያልሆኑት 16 የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲና 46 የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሠራተኞች ናቸው፡፡

ኮሚሽኑ እንዳለው ሀብት እንዲመዘገብ ማድረግ፣ የተመዘገበ ሀብት ለህዝብና አግባብ ላላቸው አካልት መረጃ መስጠት እና የተመዘገበ ሀብትን ትክክለኛነት ማረጋገጥ የሀብት ምዝገባ መሰረታዊ ጉዳዮች ናቸው እንደሆነ በመጥቀስ፣ ሀብትን አለማስመዝገብ እና ሆን ብሎ የተሳሳተ መረጃ መስጠት የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ ተሻሽሎ በወጣው አዋጅ 881/2007 አንቀጽ 19 ንዑስ አንቀጽ 2 መሰረት በሙስና ወንጀል ህግ እንደሚያስጠይቅ አሳውቋል፡፡

ይህን በማስመልከትም ኮሚሽኑ ከዚህ በፊት የሰጠውን የሀብት ማስመዝገብ የጊዜ ገደብ ተጠቅመው ለማስመዘገብ ፈቃደኛ ያልሆኑ አካላትን መረጃና ማስረጃ በማጠናቀር የመክሰስና የመመርመር ሥልጣን ለተሰጣቸው አካላት ለመላክ የማጣራት ስራ እየተሰራ መሆኑን የኮሚሽኑ ዳይሬክተር ለሚዲያዎች ገልፀዋል፡፡

ከዚህ ጎን ለጎን የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች እንዳይደራጁና ሥራቸውን በአግባቡ እንዳይፈፅሙ ኮሚሽኑ የሚቀጥራቸውን ሠራተኞች ባለመቀበል፤ ደመወዝ ባለመክፈል፣ የሥራ ቢሮ ባለመስጠት እና መሰል አላስፈላጊ ድርጊቶችን የሚሰሩ ተቋማትን ተጠያቂ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ዳይሬክተሩ መጠቆማቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img