Thursday, October 17, 2024
spot_img

ሩስያ በኢትዮጵያ ደም መፋሰሱን ለመግታት ብቸኛው መፍትሔ የተኩስ አቁም ነው አለች

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ነሐሴ 14፣ 2013 ― የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ እየተከታተለች እንደምትገኝ ያመለከተችው ሩስያ፣ ደም መፋሰሱን ለመግታት እና የሰብአዊ አቅርቦትን ለማሻሻል ብቸኛው መፍትሔ የተኩስ አቁም መሆኑን ገልጻለች፡፡

በአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የትዊተር ገጽ ላይ በቃል አቀባዩዋ ማሪያ ዣካሮቫ በኩል በተነበበው መልእክት፣ ሩስያ በኢትዮጵያ በመንግስት ጦር እና በሕወሓት መካከል የቀጠለውን ጦርነት አገሪቱ እየተከታተለች ስለመሆኑም ሰፍሯል፡፡

ዘጠኝ ወራት ወራት ባስቆጠረው በፌዴራል መንግሥት እና በሕወሓት ኃይሎች መካከል በሚደረገው ጦርነት፣ በመንግስት በኩል ከሰኔ 21፣ 2013 ጀምሮ የተናጠል የተኩስ አቁም ታውጆ መከላከያ የመቐለ ከተማን ለቆ የወጣ ቢሆንም፣ በሕወሓት በኩል የተኩስ አቁሙን ለመቀበል በመጀመሪያ ሰባት ቀጥሎም አምስት ቅድመ ሁኔታዎች መቀመጣቸው ይታወቃል፡፡

በትግራይ ክልል የጀመረው ጦርነት በአሁኑ ወቅት ሕወሓት ወደ አጎራባች አማራ እና አፋር ክልሎች በመግፋቱ ተዛምቶ መቀጠሉን በየለቱ የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img