Tuesday, October 15, 2024
spot_img

በኢትዮጵያ ተፋላሚ ኃይሎች ለሰላማዊ አማራጭ ዕድል እንዲሰጡ የተመድ ዋና ጸሐፊ ጠየቁ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ነሐሴ 14፣ 2013 ― የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ጸሐፊ አንቶንዮ ጉቴሬዝ በኢትዮጵያ ጦርነት ተፋላሚ ኃይሎች ለሰማላዊ አማራጭ እድል እንዲሰጡ ጠይቀዋል፡፡

ዋና ጸሐፊው ትላንት ምሽት የዓለም የሰብአዊነት ቀንን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ላይ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ ያነሱ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ በርካቶች በጦርነት ሰበብ አስከፊ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙም አስታውቀዋል፡፡

በዚሁ መግለጫቸው አለ ያሉት አስከፊ ሁኔታ አሁኑኑ ሊያበቃ ይገባል ሲሉ የተደመጡት አንቶንዮ ጉቴሬስ፣ ተፋላሚ ኃይሎች ለችግሩ ወታደራዊ አማራጭ መፍትሔ እንደማያመጣ ሊገነዘቡ እንደሚገባም ነው የገለጹት፡፡ አክለውም ለቀጣናው እና ከዚያም ባለፈ ወሳኝ ነው ያሉትን የኢትዮጵያን አንድነት እና መረጋጋት መጠበቅ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ያለው ቀውስ እንዲፈታም፣ ኢትዮጵያውያን በራሳቸው የተመራ ፖለቲካዊ ውይይት እንዲጀምሩ መፍቀድ እንደሚያስፈልግ ዋና ጸሐፊው ጠይቀዋል፡፡

አንቶንዮ ጉቴሬዝ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኢትዮጵያውያን በመሃላቸው ሰላም እንዲሰፍን እና ወደ እርቅ እንዲመጡ ከአፍሪካ ሕብረት እንዲሁም ከሌሎች አገሮች ጋር በመሆን እንደሚሠራም ገልጸዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img