Thursday, October 17, 2024
spot_img

ሕወሓት ወደ ደብረታቦር ከተማ ከባድ መሳሪያዎችን በመተኮስ ንጹሐን ላይ ጥቃት መፈጸሙን የከተማው ተቀዳሚ ከንቲባ ገለጹ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ነሐሴ 14፣ 2013 ― ሕወሓት በትላትናው እለት በአማራ ክልል ወደምትገኘው ደብረታቦር ከተማ አራት ከባድ መሳሪያዎችን በመተኮስ ንጹሐን ላይ ጥቃት መፈጸሙን የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ከንቲባ ወንዴ መሰረት ገልጸዋል።

እንደ ከንቲባው ከሆነ በጥቃቱ በቤት ውስጥ የነበሩ 5 ሰዎች ላይ የሞት፣ በ2 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት እንደደረሰና ግምቱ ያልታወቀ የግለሰቦች ቤትም ወድሟል፡፡

በጥቃቱ የሞቱት የአንድ ቤተሰብ አባላት 3 ሴቶችና 2 ወንዶች ናቸው የተባለ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ አንድ ሕጻን እንደሚገኝበት መግለጻቸውን የዘገበው አማራ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img