Saturday, October 5, 2024
spot_img

በአዲስ አበባ ጎርፍ የሰባት ሰዎችን ሕይወት ነጠቀ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ነሐሴ 12፣ 2013 ― በትላንትናው እለት በአዲስ አበባ ዝናብ ባስከተለው ከባድ ጎርፍ በተለይ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በመካነየሱስ ሴሚናር ቤተክርስቲያን አካባቢ የሰባት ሰዎችን ህይወት ተነጥቋል፡፡

ይህንኑ ያስታወቁት የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ አደጋ የደረሰባቸውን የከተማውን አካባቢዎች ተዘዋውረው መመልከታቸውንም ገልጸዋል፡፡

በጎርፍ አደጋው ውድ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች ልባዊ መፅናናትን የተመኙት ወይዘሮ አዳነች፣ የከተማው አስተዳደርና ነዋሪ ተጎጂዎችን መልሶ በማቋቋም በሁለንተናዊ መልኩ ከጎናችሁ ይቆማል ብለዋል፡፡

አክለውም በቀጣይ ቀናት ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ ስለሚጠበቅ በሁሉም አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች በየአካባቢያቸው አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡

በአዲስ አበባ በትላናትናው እለት ከባድ ጎርፍ ካስተናገዱ ሰፈሮች ውስጥ አስኮ፣ አደይ አበባ፣ በጀርመን አደባባይና በጎልፍ ክለብ አካባቢ ይጠቀሳሉ፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img