Wednesday, October 9, 2024
spot_img

የሕወሃት ታጣቂዎች በአማራ ክልል ሰላማዊ ሕዝብ ላይ ዓለም አቀፍ የጦር ወንጀል ሳይፈጽሙ እንዳልቀረ ተዘገበ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ነሐሴ 12፣ 2013 ― የሕወሃት ታጣቂዎች በአማራ ክልል ሰላማዊ ሕዝብ ላይ ፈጽመውታል በተባለ የበቀል ጥቃት ዓለም አቀፍ የጦር ወንጀል ሳይፈጽሙ እንዳልቀረ የእንግሊዙ ቴሌግራፍ ጋዜጣ ይዞት በወጣው የምርመራው ዘገባ አመልክቷል፡፡

የሕወሃት ተዋጊዎቹ በሐምሌ ወር መገባደጃ ግድም ፈጽመውታል በተባለው ጥቃት፣ በሰሜን ወሎ ዞን የገጠር መንደሮችን በከባድ መሳሪያ ከደበደቡ በኋላ ቤት ለቤት እየዞሩ ያገኙትን ሰላማዊ ሰው እንደረሸኑ በዘገባው ላይ የተጠቀሱ የዓይን እማኞች ተናግረዋል፡፡

ኃይሎቹ በአፋር ክልል ድንበር አቅራቢያ ባለች የገጠር መንደር በትንሹ 50 መኖሪያ ቤቶችን ሙሉ በሙሉ በእሳት እንዳቃጠሉ ከሳተላይት ምስሎች ማረጋገጥ እንደተቻለ የጠቀሰው ዘገባው፣ መንደሮቹ በተቃጠሉበት ወቅት ግን በአካባቢው ጦርነት ስለመካሄዱ ማስረጃ የለም ብሏል፡፡

በዚሁ ጥቃት እስከ 100 የሚገመቱ ሰዎች ሳይገደሉ እንዳልቀሩ ነው የተገመተ ሲሆን፣ ቴሌግራፍ ቁጥሩን ከአማራ ክልል ሹማምንት ለማረጋገጥ የመገናኛ ዘዴዎች መቋረጥ እንቅፋት እንደሆነበት ነው ያመለከተው፡፡

ይኸው ጥቃት ተፈጽሟል በተባለበት ወቅት የፌዴራል ሠራዊት ሥፍራውን ለቆ ወጥቶ ስለነበር ነዋሪዎችን የሚከላከላቸው እንዳልነበረና በአንዳንድ አካባቢዎች ነዋሪዎች ራሳቸውን ለመከላከል ጠብመንጃ ቢያነሱም፣ የሕወሓት ኃይሎች በአጸፋው በሕዝብ ላይ እንደተኮሱና የእርሻ መሬት እንዲሁም ቤታቸውን አቃጥለዋል፡፡

ቴሌግራፍ ዲኤክስ ኦፕን በተባለ የእንግሊዝ የምርመራ እና ትንተና ድርጅት አስደረግኩት ባለው ማጣራት በአፋር ክልል አዋሳኝ ላይ የሚገኝ አጋምሳ የተሰኘ መንደር ሙሉ ለሙሉ ወድሟል፡፡

በዘገባው የሕወሓት ኃይሎች ቃል አቀባይ እንደሆነ የተገለጸው ፍሥሐ ተሰማ የተባለ ግለሰብ ጋዜጣው አገኘሁት ያለውን የምርመራ ግኝት ማስተባበሉ ተጠቅሷል፡፡

ከስምንት ወራት በፊት በትግራይ ክልል የጀመረው የፌዴራል መንግስት እና የሕወሓት ኃይሎች የተቀሰቀሰው ጦርነት በቅርብ ጊዜያት ወደ አጎራባች ክልሎች መስፋፋቱ ይታወቃል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img