አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ነሐሴ 12፣ 2013 ― በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጁትን ሕወሃት እና መንግስት ‹‹ሸኔ›› የሚለውና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት በሚል የሚጠራውን ቡድን የሚያወግዝ ሰልፍ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ስለመሆኑ የመንግስት ሚዲያዎች ዘገባ ያመለክታል፡፡
በተቃውሞ ሰልፉ ላይ ‹‹ሸኔ እና ህወሃት የኢትዮጵያ ህዝብ ታሪካዊ ጠላቶች ናቸው››፣ ‹‹ለኢትዮጵያ ሰላምና አንድነት ዘብ እንቆማለን›› የሚሉና ቡድኖቹን የሚያወግዙ መፈክሮች መስተጋባታቸው ተመላክቷል፡፡
በተመሳሳይ የቢሾፍቱ ከተማ ነዋሪዎችም ህወሃት እና ሸኔ የሽብር ቡድኖችን የሚያወግዝ ሰልፍ እያደረጉ እንደሚገኙ የሚያመለክቱ የፎ መረጃዎች ወጥተዋል፡፡