ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ በአስኮ፣ በአደይ አበባ፣ በጀርመን አደባባይና በጎልፍ ክለብ አካባቢ በደረሰ ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ እስከአሁን ድረስ መንገዶች ጭምር መዘጋጋታቸው የተገለጸ ሲሆን፣ የድንገተኛና የእሳት አደጋ ሰራተኞች በቦታዎቹ በመገኘት የከፋ ሰብዓዊ ጉዳት እንዳይደርስ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸውን የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።
ተጎጂዎችንም ወደ ህክምና መስጫ በማጓጓዝ እና የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ምክትል ከንቲባዋ አክለዋል።
ወይዘሮ አዳነች በመጪዎቹ ቀናት ከፍተኛ መጠን ያለው የዝናብ ስርጭት ስለሚኖር ነዋሪዎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።