Sunday, October 13, 2024
spot_img

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ነገ ወደ ቱርክ ያቀናሉ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ነሐሴ 11፣ 2013 ― ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከቱርኩ ፕሬዝደንት ረጀብ ጠይብ ኤርዶጋን በቀረበላቸው ግብዣ መሠረት ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ነገ ወደ ቱርክ እንደሚያቀኑ የቱርክ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን መስሪያ ቤት ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ይህ ጉብኝት የሀገራቱ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረበትን 125ኛ ዓመት የሚዘክር እንደሆነም ተገልጿል።

መሪዎቹ በሀገራቱ ሁለትዮሽ ግንኙነት ሁለንተናዊ ገፅታዎች፣ ትብብርን ለማጠንከር ሊወሰዱ በሚገባቸው እርምጃዎች ላይ እንዲሁም ዓለም አቀፋዊና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img