Wednesday, October 16, 2024
spot_img

የመንግሥታቱ ድርጅት አጋሮቹ በትግራይ ጦርነት ወገንተኛ የፖለቲካ አጀንዳዎችን ያራምዳሉ መባሉ አሳስቦኛል አለ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ነሐሴ 11፣ 2013 ― የተባበሩት መንግሥታት ቅርንጫፍ ድርጅቶችና የሰብዓዊ ረድዔት አጋሮቹ በኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ጦርነት ወገንተኛ የፖለቲካ አጀንዳዎችን ያራምዳሉ መባሉ እጅጉን እንዳሳሰበው ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል፡፡

ይህ ሁኔታ በቅርቡ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃንና በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተንፀባረቀ መሆኑን መግለጫው አንስቷል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም ሆነ የረድዔት እርዳታ ድርጅቶች ሰብዓዊ እርዳታን ሲለግሱ አራት የሰብዓዊነት መርሆችን ተከትለው ነው ያለው መግለጫው፣ እነዚህም ሰብዓዊነት፣ ገለልተኝነት፣ ነፃነት ከአድልዎ ነፃ በሆነ መልኩ ነው ሲል አስፍሯል፡፡

እነዚህን መርሆዎች በማክበር እና ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በመቀናጀት ድርጅቱ እና አጋሮቹ በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎችና የከተማ አስተዳደደሮች ለተቸገሩ ነዋሪዎች አስፈላጊውን እርዳታ እያደረገ እንደሚገኝ ጠቅሷል።

እርዳታውንም እያደረገ የሚገኘውም ተጎጂውን ህዝብ ማዕከል ባደረገ መልኩ ነፃና ገለልተኛ በሆነ መልኩ ነው ብሏል።

ከዚህ ቀደም የፌደራል መንግሥት ከሰብዓዊ አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች ጋር ተቀራርቦ ለመስራት ፈቃደኛ ቢሆንም ‹‹አንዳንድ ዘገባዎች በስህተትም ይሁን በሌላ መንገድ ወደ ትግራይ የሚገቡ በረራዎችን መንግሥት እያስተጓጓለ ያለ ይመስል ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰቡ የተሳሳተ መረጃ እየሰጡ ነው›› ሲል አንዳንድ ድርጅቶችን ከሶ ነበር፡፡

በተመሳሳይ የፌደራል መንግሥት የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (ዩኤን ኦቻ) የትግራይ ክልልን በተመለከተ ‹‹የተሳሳቱ ዘገባዎችና መግለጫዎችን›› እያቀረበ እንደሆነና ይህም አጋዥና ገንቢ አይደለምም ሲል መውቀሱ አይዘነጋም፡፡

ከዚህም ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ መንግሥት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (ዩኤን ኦቻ) አገሪቷ ከአውሮፓ 1986 ጀምሮ ከድርጅቱ ጋር ከገነባችው ፍሬያማ ግንኙነት ጋር የማይመጣጠኑ ተግባራትን እየፈፀመ ነው ሲልም ለተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ደብዳቤ ልኮ ነበር፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img